Our vision
Our Vision is to become outstanding and prefered procurement and property disposal service provider in Ethiopia.
Related offices
Legal Documents Related to Procurement and Property Administration
Web Content Display
Welcome to our website Thank you for visiting us ....
We Perform procurement of public organizations common user items and nationally strategic utilities; render efficient and effective property disposal service; including support for the private sector.
To Browse newly invted Bid Click here.
እንኳን ወደ ድረገፃችን በሰላም መጡ!... ስለ ጉብኝትዎ እናመሰግናለን።
የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ሐምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሲቋቋም ዓላማዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን የመንግስት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡
የቅርብ ጊዜ ጨረታዎች
ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ 08_06_2014
ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ 08_06_2014 (Version 1.0)


Version 1.0
የጨረታ ማስታወቂያ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር PPS/VP- 3FBI/08/05/2014 የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የግብርና ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በግብርና ሚኒስቴር የብሄራዊ እንስሳት ጤና ምርምርና ጥናት ማዕከል ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡ 1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣ 3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣ 4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፣ 5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ(20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ 6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣ 7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል:: 8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡ 9. አገልግሎቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡ 10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ 11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122 37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣ 12. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣ መንግሥት ግዥ አገልግሎት አዲስ አበባ
