News News

Back

የመንግስት ግዥ አገልግሎት የተገልጋዮች ቻርተር

 

                                            

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት

የተገልጋዮች ቻርተር

 

ጥቅምት፣ 2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ

እንኳን ወደ ተቋማችን አገልግሎት ለማግኘት በደህና መጣችሁ

 

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር

በሀገራችን በየዓመቱ ከሚመድበው በጀት ውስጥ አብዛኛው በተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ ላይ እንደሚውል ይታወቃል፡፡ የመንግሥት መ/ቤቶች የሚጠቀሙባቸው ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ለማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸው የመንግሥት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ለማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ለማድረግ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ተቋቁሞ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

አገልግሎቱ በ2017 ዓ.ም በአገሪቱ ውስጥ የላቀና ተመራጭ የግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆንን ራዕይ ሰንቆ የሚሰራ ሲሆን ሥራ ከጀመረበት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የብረት፣ የስንዴ፣የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የህንጻ ግንባታ፣ ለመማር ማስተማሩ የሚያገለግሉ ማጣቀሻ መጽሃፍት፣ የላብራቶሪና የመመገቢያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች ግዥ እንዲሁም የማዕቀፍ ስምምነት ግዥዎችን የፈፀመ ሲሆን የተለያዩ ዕቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ቶነሮችን በሽያጭ በማስወገድ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡ 

አገልግሎቱ የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት የወቅቱን የህብረተሰብ ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ለመስጠት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም አገልግሎቱ በዚህ የዜጎች ቻርተር ላይ በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን እርካታ እያሳደገ እንደሚሄድ ያለኝን ፅኑ እምነት እየገለጽኩ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ያላችሁን ገንቢ አስተያየት በመስጠት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡     

 

 

 

 

 

ማውጫ

መግቢያ

1 . የተቋሙ ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች

2. ተልዕኮ

3. ራዕይ

4. የተቋሙ እሴቶች

5.  የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

6.  የተቋሙ ዋና ዋና ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት - 

6.1 ተገልጋዮች

6.2 ባለድርሻ አካላት

7. በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ

8. የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚዎች መብቶች

9. ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ማሟላት የሚኖርባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

10. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓታችን

10.1  ቅሬታና አቤቱታ የማቅረቢያ ጊዜ ገደብ

10.2 ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን ስለማጣራት

10.3 ስለቅሬታና አቤቱታዎች መልስ አሰጣጥ

11. አስተያየትናግብረመልስመቀበያስርዓታችን 

12. የክትትልና ግምገማ ስርዓታችን 

13.  የመረጃ ስርጭት ዘዴዎቻችን 

ወቅታዊ መረጃዎችን 

ሪፖርቶች

14 . ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ድጋፍ የሚሰጡና የቅንጅት ስራ የሚጠይቁ /ቤቶች

አድራሻዎቻችን 

 

መግቢያ

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የመንግሥት መ/ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ እቃዎች እና ስትራቴጂካዊ 

ጠቀሜታ  ያላቸውን ግዥዎችን የሚፈጽም እንዲሁም በየመስርያቤቱ ተከማችተው ሚገኙ የሚወገዱ ንብረቶችን በማስወገድ ሃገራዊ ኢኮኖሚያዊ ወጪን ለማዳን በሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 የተቋቋመ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ነው፡፡የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም በሁሉም አገሪቷ የአስተዳደር እርከኖች በተሟላ መልኩ እንዲተገበር፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ሀገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ሥር እንዲሰድና አገልግሎት አሰጣጥም ቀልጣፋና ውጤታማ፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት ባለው አሰራር እንዲመራ መንግስት ፖሊሲ ቀይሶና ለፖሊሲው ማስፈፀሚያ የተለያዩ ስትራቴጂክ ዕቅዶች በመንደፍ በመተግበር ላይ ነው፡፡ ከዚህ  አኳያ አገልግሎቱ

የተገልጋዮች ፍላጎት በተገቢው መንገድ በማሟላት አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ፍትሃዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡በመሆኑም ተቋሙ 

የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተገልጋይ ተኮር የሆኑና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የመንግሥት የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ ማኑዋል መሰረት በማድረግ ይህን የዜጎችና ተገልጋዮች የአገልግሎት አሰጣጥ ቻርተር አዘጋጅቷል፡፡ ቻርተሩ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን፣ የአገልግሎት መስፈርቶችን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዶችን በማስተዋወቅ ግልጽነትን፣ ውጤታማነትንና ተጠያቂነት ያሰፍናል ተብሎ ይታመናል፡፡ይህንን መሠረት በማድረግ የተገልጋዮችና የባለድርሻ አካላት እርካታ ለማረጋገጥ ቀደም ሲል ተዘጋጅቶ የነበረውን የዜጎች ቻርተር በማሻሻል እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

 

 1.   የተቋሙ  ተልዕኮ

 

የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃዎች እና አገራዊ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ግዥዎች መፈጸም፣ ቀልጣፋና ዉጤታማ የንብረት ማስወገድ አገልግሎት መስጠት፣ እንዲሁም ለግሉ ዘርፍ ጭምር እገዛ ማድረግ፣

 1.   የተቋሙ  ራዕይ

 

በ2017 ዓ.ም በአገሪቱ ውስጥ የላቀና ተመራጭ የግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆን፣

 1. የተቋሙ እሴቶች

 

 • የተገልጋይ ተኮር አገልግሎት፣
 • ግልጽነትና ተጠያቂነትን ፣
 • ህግ ደንብና መመሪያ ለዉጤት፣
 • በቡድን  መስራት፣
 • ሙስናን መፀየፍ ፣
 • የመማማርና የመለወጥ ተነሳሽነት፣

4.የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

 • ለፌዴራል መንግስት መ/ቤቶች እንዲሁም ጥያቄ ሲቀርብ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ለክልል መንግስታትና ለከተማ አስተዳደሮች የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የእቃም ሆነ የአገልግሎት ግዥ እንፈጽማለን፣
 • የግዥ ውሎችን ማስተዳደር (መከታተል እና ማስፈፀም)፣
 • በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸው የመንግሥት መ/ቤቶች ንብረቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በጨረታ እናስወግዳለን፣
 • በግዥ አፈጻጸምና በንብረት አወጋገድ ላይ ምክር፣ ስልጠ እና ድጋፍ መስጠት፣
 • የሚገዙና የሚወገዱ ንብረቶችን አስመልክቶ መረጃ መስጠት፡፡

5.የተቋሙ ዋና ዋና ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት

5.1 ተገልጋዮች

 • የፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች፣
 • የአቅራቢ ንግድ ድርጅቶች፣የግሉ ዘርፍ (ድርጅቶችና ግለሰቦች)፣
 • የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣
 • የክልል መንግስታት፣
 • አገልግሎትና መረጃ ፈላጊ ዜጎች፣
 • የብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች፣
 • የፌዴራል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
 • የከተማ መስተዳደሮች፣
 • የአገልግሎቱ ሠራተኞች ናቸው፡፡

5.2 ባለድርሻ አካለት

 • የስራ አመራር ቦርድ፣
 • የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣
 • የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣
 • የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣
 • የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣
 • የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር፣
 • የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣
 • የኢትዮጵያ የባህር ትራንዚትና ሎጀስቲክ አገልግሎት፣
 • ሌሎች የትራንስፖርትና የሎጀስቲክ ድርጅቶች፣
 • የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣
 • የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣
 • የብረታ ብረት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣
 • ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣
 • የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣
 • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣
 • የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ፣
 • የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣
 • የአካባቢ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር፡፡
 

 

6.በተቋሙ  የሚሰጡ  አገልግሎቶች  የአገልግሎት  አሰጣጥ  ስታንዳርድ

    

.ቁ

የሚሰጡ አገልግሎቶች

አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ

የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

ጊዜ

የሚሰጥበት ሁኔታ

6.1

ግዥ ዳይሬክቶሬት

 

 

 

 

6.1.1

የተመሳሳይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች - (የማእቀፍ ስምምነት) ግዥ አገልግሎት መስጠት

ሂደቱ

 

 

 

 

6.1.1.1

 ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስ ያልሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

202 ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

ተጠቃሚ መ/ቤቶች ዝርዝር የግዥ ፍላጐት መግለጫዎችንና የተያዘዉን  በጀት በወቅቱ መላክ ይጠበቅባቸዋል

 

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስብ የሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

217 ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

6.1.1.2

 አለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስ ያልሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

222 ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

ተጠቃሚ መ/ቤቶች ዝርዝር የግዥ ፍላጐት መግለጫዎችንና የተያዘዉን  በጀት በወቅቱ መላክ ይጠበቅባቸዋል

6.1.1.3

 አለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስብ የሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

232 ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

ተጠቃሚ መ/ቤቶች ዝርዝር የግዥ ፍላጐት መግለጫዎችንና የተያዘዉን  በጀት በወቅቱ መላክ ይጠበቅባቸዋል

6.1.2

አገራዊ ስትራቴጂክ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ ማከናወን

ሂደቱ

 

 

 

 

6.1.2.1

 ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስ ያልሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

116  ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

የፌዴራል ባለበጀትመ/ቤቶች በተመረጡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ላይ የሚፈልጉትን የዕቃ መጠን በወቅቱ ማሳወቅ

6.1.2.2

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስብ የሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

131 ቀናት

ሠነድ/በደብዳቤ

የፌዴራል ባለበጀትመ/ቤቶች በተመረጡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ላይ የሚፈልጉትን የዕቃ መጠን በወቅቱ ማሳወቅ

6.1.2.3

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለግንባታ ግዥ

(ውስብስብ ላልሆነ)

 

በግዥ ዳይሬክቶሬት

122 ቀናት

ሠነድ/በደብዳቤ

የፌዴራል ባለበጀትመ/ቤቶች በተመረጡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ላይ የሚፈልጉትን የዕቃ መጠን በወቅቱ ማሳወቅ

6.1.2.4

 አለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስ ያልሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

136 ቀናት

በሠነድ/በደብዳቤ

የፌዴራል ባለበጀትመ/ቤቶች በተመረጡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ላይ የሚፈልጉትን የዕቃ መጠን በወቅቱ ማሳወቅ

6.1.2.5

አለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ

(ውስብስብ የሆነ)

በግዥ ዳይሬክቶሬት

146 ቀናት

ሠነድ/በደብዳቤ

የፌዴራል ባለበጀትመ/ቤቶች በተመረጡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ላይ የሚፈልጉትን የዕቃ መጠን በወቅቱ ማሳወቅ

6.2

ውል አስተዳደር ዳሬክቶሬት

6.2.1

የውል ሠነድ ዝግጅት

 

 

 

 

6.2.1.1

ለብሄራዊ/ለአለም አቀፍ/ለማዕቀፍ  ግልጽ ጨረታ

 

በውል ዳይሬክቶሬት

6 ቀን

በሰነድ

የጨረታ አሸናፊነት መግለጫ ግልባጭ መደረግ

 

6.2.2

የማዕቀፍ ስምምነት ግዥ ውል ማከናወን

 

 

 

 

6.2.2.1

ከውል አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ከተለያዩ የፌዴራል መስርያ ቤቶች/ዩኒቨርሲቲዎች እና አቅራቢዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ መስጠት

በውል ዳይሬክቶሬት

ከ2 ሰዓት-10 ቀናት

 

የቀረበ ቅሬታ

6.2.3

የስትራሬጂያዊና ሌሎች ውል ማከናወን

 

 

 

 

6.2.3.1

ኤል ሲ እንዲከፈት ማድረግ

በውል ዳይሬክቶሬት

35 ቀናት

 

የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ማግኘት

የውል ማስከበርያ ሰነድ

ፕሮፎርማ ኢንቮይስ

የማሪን ኢንሹራንስ

ለኤልሲ መክፈቻና ለባንክ ኮሚሽን የሚሆን ገንዘብ ወደ ፑል አካውንት እንዲዛወር ማድግ

ከዴሊኩዎንሲ ዝርዝር ነጻ መሆን

 

6.2.3.2

ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን ገቢ ማድረግ 

በውል ዳይሬክቶሬት

15 ቀን

 

ውል

የጭነት

የቀረጥ ክፍያ

የአገልግሎት ክፍያ

የኮንቴይነር ሪሊዝ እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው ፈቃዶች

6.2.3.3

ለአቅራቢ ድርጅት ክፍያ እንዲለቀቀለት ማድረግ

 

 

 

ውል

የጭነት ሰነዶች

የቀረጥ ክፍያ

የአገልግሎት ክፍያ

የኮንቴነር ሪሊዝ እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው ፍቃዶች

6.2.3.4

ተጠቃሚ መስርያ ቤቶች ለግዥ አገልግሎት ወደ አገልግሎታችን ባንክ ሂሳብ ገቢ ካደረጉት ገንዘብ ተመላሽ/ተፈላጊ ካለ ማሰወቅ

 

 

 

ውል

ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት  የቀረበ የሂሳብ ሪፖርት

6.3

የገበያ ጥናት መረጃ ዳይሬክቶሬት

 

 

6.3.1

በማዕቀፍ ለሚገዙ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የሚደረግ የገበያ ዋጋ ጥናት ማካሄድ

ገ/ጥ/መ/ዳይሬክቶሬት

6 ቀን

በሰነድ/በአካል በመገኘት/ በደብዳቤ

የገበያ ዋጋ ይጠናልን ጥያቄ

6.3.2

በሽያጭ ለሚወገዱ ንብረቶች የመተኪያ ዋጋ ጥናት ማካሄድ

ገ/ጥ/መ/ዳይሬክቶሬት

4 ቀን

በሰነድ/በአካል/

በደብዳቤ

የመተኪያ ዋጋ ይጠናልን ጥያቄ

6.3.3

የዋጋ ማስተካከያ ለሚጠይቁ አቅራቢዎች ማስተካከያን ጥናት በማድረግ ማዘጋጀት

ገ/ጥ/መ/ዳይሬክቶሬት

8 ቀናት

በደብዳቤ/በአካል

ከአቅራቢዎች የሚመጣ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ

6.3.4

በማዕቀፍና በስትራቴጂክ የሚገዙ ግዥዎችና የሚወገዱ ንብረቶችን መረጃ ማደራጀትና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት

ገ/ጥ/መ/ዳይሬክቶሬት

21 ቀናት

በሰነድ/በደብዳቤ/በአካል

የተጠናቀቁ ግዢዎችና በሽያጭ የተወገዱ ንብረቶች በሚኖሩበት ወቅት እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ ሲጠየቅ

6.4

የንብረት ዋጋ ግምትና ማስወገድ ዳይሬክቶሬት

 

 

6.4.1

ያለአገልግሎት በፌዴራል መ/ቤቶች የተከማቹ ንብረቶች ማስወገድ

ን/ዋ/ግ/ማ/ዳይሬክቶሬት

44 ቀናት

በአካል

 

 

 

 

 

 

 

መ/ቤቶች ጥያቄ ሲያቀንርቡ

6.4.2

ለመ/ቤቶች በንብረት አወጋገድ ዙርያ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት

 

በአካል

አገልግሎቱ በሚጠይቀው መ/ቤት

1 ቀን

እንደ አስፈላጊነቱ

በደብዳቤ

ን/ዋ/ግ/ማ/ዳይሬክቶሬት

2 ሰአት

በደብዳቤ

በስልክ

ን/ዋ/ግ/ማ/ዳይሬክቶሬት

5-10 ደቂቃ

በቃል

ስልጠና በመስጠት

አገልግሎቱን በሚጠይቀው መ/ቤት ይወሰናል

1-3 ቀን

በስልጠና ማንዋል

6.4.3

የተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ  ሠነድ ማዘጋጀት

የንብረት ማስወገድ ባለሙያዎች

5 ቀናት

በሰነድ/በደብዳቤ

የጨረታ ዋጋ መነሻ ግምት ሲጠናቀቅ

6.4.4

የተሸጡት ንብረቶች መነሳታቸው መከታተል

‘’

10 ቀናት

በደብዳቤ/በስልክና በአካል እንደ አስፈላጊነቱ

ሙሉ ክፍያ ያልከፈሉ ተጫራቾችን ዝርዝር ከፋይናንስ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሲላክ

 

7.የአገልግሎቶቻችን  ተጠቃሚዎች  መብቶች

 

ሀ. ሀብትና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሁም ግልጽ አሰራር መሠረት ያደረገ የግዥ አፈጻጸም አገልግሎት የማግኘት፣

ለ. ተደራሽ የሆነ የግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የማግኘት፣

ሐ. በተፈረመው ውል መሠረት አገልግሎት የማግኘት መብት ፣

መ. የምክርና ሙያዊ ድጋፍ የማግኘት፣

ሰ. ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ፣

ረ. ላቀረቡት ቅሬታ ወይም አቤቱታ ፍትሃዊ ምላሽ የማግኘት፣

ሠ. አገልግሎቱ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መከናወኑን የመከታተል፣አስተያየት የመስጠት፣የመተቸት፣የመገምገም፤

ሸ. በቂና ወቅታዊ ምላሽ ባጡበት ጊዜ ለሚዲያ፣ ለሕዝብ እምባ ጠባቂ፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የማሳወቅ፣

 

 

8.ተጠቃሚዎች  አገልግሎቱን  ለማግኘት  ማሟላት  የሚኖርባቸው  ቅድመ  ሁኔታዎች

.ቁ

የአገልግሎት ዓይነት

አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎችና ቅድመ ሁኔታዎች

 

 

አቅራቢ ድርጅቶች

ባለበጀት መ/ቤቶ

1

አገራዊስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ዕቃዎች ግዥ ማከናወን እና ለፌዴራል መንግስት መ/ቤቶች እንዲሁም ጥያቄ ሲቀርብ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ለክልል መንግስታትና ለከተማ አስተዳደሮች የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ግዥ እናካሂዳለን፣

 • አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በወቅቱ ማብራሪያ መስጠት፣
 • የተሸጠውን ጨረታ ሰነድ መሠረት ያደረገ ግልጽ የመጫረቻ ሰነድ እና ህጋዊ ዶክመንቶች ማቅረብ፣
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ናሙና ማቅረብ፣
 • ጥራትያላቸውዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በውሉ  በተገለጸው ጊዜ መሠረት ማቅረብ፣
 • ከብልሹ አሠራር የጸዳ መሆን፣
 • ውል መፈረምና ማክበር፣
 • ክፍያቸውን በመመሪያው መሰረት መውሰድ
 • የተሟላ የግዥ ፍላጎት ዝርዝር መረጃ ማቅረብ፣
 • ግልጽ የግዥ ፍላጎት መግለጫ/Specification/ ማቅረብ፣
 • የቴክኒክ ግምገማዎች ላይ ሙያዊ እገዛ ማድረግ
 • ለግዥ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በወቅቱ ገቢ ማድረግ፣
 • የተገዙ ንብረቶችን በወቅቱ መረከብ፣
 • አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በወቅቱ ማብራሪያ መስጠት፣

 

 

 

ተ.ቁ

የአገልግሎት ዓይነት

አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎችና ቅድመ ሁኔታዎች

 

የግሉ ዘርፍ (ድርጅቶችና ግለሰቦች)፤

ባለበጀት መ/ቤቶ

2

በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውየመንግሥት መ/ቤቶች ንብረቶች እንዲወገዱ እናደርጋለን፣

 • አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት፣
 • የጨረታ ሰነድ መግዛት፣
 • ህጎችንና ደንቦችን ማክበር፣
 • ግልጽ የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ፣
 • ከብልሹ አሰራር የጸዳ መሆን፣
 • ውል መፈረምና ማክበር፣

 

 • የሚወገዱ ንብረቶች ትክክለኛና የተረጋገጠ ዝርዝር መረጃ፣
 • በጨረታ የተወገዱ ንብረቶች ለአሸናፊ ተጫራቾች በወቅቱ  ማስረከብ፣
 • በሚወገዱ ንብረቶች ላይ ማብራሪያ መስጠት፣
 • ከብልሹ አሰራር የጸዳ መሆን፣

 

3

በግዥ አፈጻጸምና በንብረት አወጋገድ ላይ ምክርና ስልጠና እንሰጣለን

 • ከግሉ ዘርፍ  ጥያቄ ሲቀርብ፣
 • ለሥነ-ምግባር መርሆዎች ተገዥ መሆን፣
 • ደንብና መመሪያ ማክበር፣
 • ከፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች፣ ልማት ድርጅቶች፣ ከክልል መንግስታትና ከከተማ መስተዳድሮች  ጥያቄ ሲቀርብ፣
 • ለሥነ-ምግባር መርሆዎች ተገዥ መሆን፣
 • ደንብና መመሪያ ማክበር፣

 

 

 

 
 1. የቅሬታ ወይም አቤቱታ አቀራረብ እና  አፈታት  ስርዓት

 

ቻርተሩ በተቀመጠው መሠረት አገልግሎት ያላገኘ ዜጋ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ የቅሬታው አቀራረብና አፈታት ሥርዓቱም በሚከተለው አግባብ ይሆናል፡፡

 • በሚሰጠው አገልግሎት ያልረካ ማንኛውም ተገልጋይ ቅሬታውን በራሱ ወይም በወኪሉ አማካኝነት በጽሁፍ፣ በቃል፣ ወይም በስልክ፣ በኢ-ሜይል፣ በፖስታና በመሳሰሉት ማቅረብ ይችላል፡፡

9.1 ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረቢያ ጊዜ ገደብ

 • ቅሬታ ያለው ባለጉዳይ ቅሬታ አደረሰብኝ ላለው ሠራተኛ ወይም ኃላፊ ቅሬታውን በ5 ቀን ውስጥ ለሚቀጥለው የስራ ሀላፊ ማቅረብ አለበት፡፡

9.2 የቅሬታ ወይም አቤቱታ ስለማጣራት

 • ቅሬታዎች ወይም አቤቱታዎች የሚጣሩበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ፡-
 • አቤቱታ የሚጣራበት ጊዜ አቤቱታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በ10  የስራ ቀናት መጣራት ይኖርበታል፡፡

9.3. ስለ ቅሬታ ወይም አቤቱታ መልስ አሰጣጥ

 • ለቅሬታ ወይም አቤቱታ የሚሰጥ ማንኛውም መልስ በጽሁፍ ይሆናል፡፡
 • ለቅሬታዎችና አቤቱታዎች መልስ የሚሰጥባቸው የጊዜ ገደብ በተመለከተ፡-
 • በአቤቱታ ማጣራት ደረጃ የሚሰጥ መልስ አቤቱታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት መልስ ሊሰጥ ይገባል፡፡

10.አስተያየት ና ግብረ መልስ መቀበያ ስርዓ

 • አስተያየት፣ ጥቆማ፣ ጥያቄና ማብራሪያ የሚሹ ዜጎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መንገዶች ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 • አገልግሎቱ በሚገኝ የአስተያየት መስጫ ሳጥን፣
 • በአካል በመገኘት፣
 • በደብዳቤዎች፣ በፖስታ ሣጥን ቁጥር          (1037)
 • በስልክ                            (0111223716)
 • በፋክስ                            (251-1-22-37-33፣251-122-37-28)
 • ዌብሳይት www.pppds.gov.et

11.የክትትል፣  ግምገማና የተጠያቂነት  ስርዓ

 

 • ተቋሙ በቻርተሩ ላይ በተቀመጠው መሠረት ዜጋው ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ስለማግኘቱ በክትትልና ድጋፍ ያረጋግጣል፣
 • በዚህም ኃላፊነት ያለባቸው የሥራ ክፍል አመራሮችና ፈፃሚዎች በቻርተሩ መሠረት ስለመፈጸማቸው የለውጥ ና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በኩል በመገምገም ሪፖርት ለአገልግሎቱ የበላይ አመራር ያቀርባሉ፣
 • በየወቅቱ በቀረቡት የክትትልና የግምገማ ሪፖርቶች ላይ በመመስረት የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፣
 • በተገኘ ክትትል ውጤት ላይ በመመስረት ስታንዳርዶችን ወቅታዊ እንዲሆኑ እና ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር እንዲዛመዱ የክለሳ ስራ ይከናወናል፣
 • የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት በአግባቡ መዘርጋቱን ያረጋግጣል፡፡

12.የመረጃ  ስርጭት  ዘዴዎቻችን

      ወቅታዊ መረጃዎችን

 • በዌብሳይት
 • በመገናኛ ብዙሃን
 • በማስታወቂያ ሰሌዳ
 • በመድረኮች
 • በዜና መጽሄት
 • በብሮሸሮች

         ሪፖርቶች

 • በጽሁፍ፣
 • በዌብሳይት፣
 • በኢ-ሜይል፣
 • በብሮሸር
 • መደበኛ የተገልጋይ መድረኮች

 

13.ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ድጋፍ የሚሰጡና የቅንጅት ስራ የሚጠይቁ መ/ቤቶች

 

ተ.ቁ

ከተቋሙ ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩ መ/ቤቶች

የሚሰጡት አገልግሎት

1

መንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣

 • የግዥና ንብረት ማስወገድ አዋጅ፣ ደንቦች፣መመሪያዎች እና ስታንዳርዶችን ማዘጋት
 • ስልጠና መስጠት

2

የብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣

 • ተቋሙ ለገባው ውል የውጭ ምንዛሬ በመፍቀድ ወይም መጠባበቂያ መያዝ እና ሌተር ኦፍ ክሬዲት መክፈት

3

መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣

 • የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪዎች ግዥን ዝርዝር ስፔስፍኬሽን ማዘጋት

4

የኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች ኤጀንሲ

 • በኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎችን ደረጃ (ስታንዳርድ) የማውጣት አገልግሎት

5

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት

 • የሚገዙ ዕቃዎችና ደረጃ (ስታንዳርድ) የማረጋገጥ አገልግሎት

6

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣

 • ከውጭ ቀረጥ መልቀቂያ (clearing)የሚገቡ ዕቃዎች  አገልግሎት

7

የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣

 • የባህርና የየብስ እና የሞተር የመድህን ዋስትና አገልግሎት

8

የኢትዮጵያ የባህር ትራንዚትና ሎጀስቲክ አገልግሎት፣

 

 • በባህርና በየብስ የተገዙ እቃዎች የማጓጓዝ አገልግሎት
 • የትራንዚትና ከስተም ክሊሪንግ አገልግሎት

9

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን

 • ወደ ሃገር ውስጥ ለሚገቡ ተሸከርካሪዎች የማስገብያ ፈቃድ መስጠት
 • ወደ ሃገር ውስጥ ለከቡ ተሸከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሸ ማድረግ

14.አድራሻዎቻችን

 

ተ. ቁ

የኃላፊ/ ባለሙያ ስም

የሥራ ኃላፊነት

 

አድራሻ

ስልክ

ኢ-ሜይል

1

 

ዋና ዳይሬክተር

0111223740

 

2

ወ/ሮ  አበባ አለማየሁ

ም/ዋና ዳይሬክተር(ግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ)

0111223729

AbebaAlemayehu68@gmail.com

 

3

አቶ ኢቲሳ ደሜ

ም/ዋና ዳይሬክተር (ንብረት ማስወገድና የገበያ ጥናት ዘርፍ)

0111223720

ettodame@gmail.com

4

አቶ ተክለብርሃን  ገ/መስቀል

የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ

0111223729

teklebrhang7@gmail.com

5

አቶ መልካሙ ደፋሊ

የኮርፖሬት ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክተር ጄኔራል

0111540392

malkamud@yahoo.com

6

አቶ ወርቁ ገዛኸኝ

 የውጭና የሀገር ውስጥ ግዥ  ዳይሬክተር

0111223722

workugezahegn1986@gmail.com

7

አቶ ሹንቃ አዱኛ

የንብረት ዋጋ ግምትና  ማሰወገድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

0111223736

shunkaadugna@gmail.com

8

አቶ ደምረው ነገሰ

የአቅም ግንባታና ድጋፍ ዳይሬክተር

0111541473

demirown837@gmail.com,

9

 

የገበያ ዋጋ  ጥናት ዳይሬክተር

0115540118

 

10

አቶ ወንድወሰን ወንጀሎ

የግዥ ቴክኒክ ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት

 

wondewosenwonjalo201@gmail.com

11

አቶ ሰለሞን  ፋንታሁን

የውል አስተዳደር  ዳይሬክተር

0111542856

soulomoon@gmail.com

12

ወ/ሮ ረድኤት ተክሉ

የእቅድ፣ በጀት ዝግጅትና የአፈፃፀም ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

0111223715

redietteklukebede@gmail.com

13

አቶ ዮሴፍ ረፊሶ

የህግና አለምአቀፍ ጉዳዮች  ዳይሬክተር

0111223727

Yosef.rafiso@yahoo.com

14

አቶ አብርሃም ወይቤ

ንብረት  አስተዳደር ና ጠቅላላ አገልግሎ ዳይሬክተር

0111542192

weibe747@gmail.com

15

ወ/ሮ  መሰረት  አፈወርቅ

የኦዲት  ዳይሬክተር 

0111223706

Meseret.afeworke@gmail.com

16

አቶ ዘሪሁን ስለሺ

የሰው ሃብት ስራ አመራርና ልማት ዳይክተር

0111223742

Zerihunsileshi2@gmail.com,
 

17

ወ/ሮ ጎጃም ታደለ

የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር

0111223706

gojamtadele@yahoo.com

18

አቶ በያን መሃመድ

የግዥና ፋይናንስ  ዳይሬክተር

0111540784

beyanmohammed1963@gmail.com

19

አቶ ምህረት ማስረሻ

የለውጥ ስራ አመራርና ቅሬታ አፈታት ዳይሬክቶሬት

0111541486

miheretmz@gmnail.com

20

አቶ ታደሰ ተክለጻድቅ

የመረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር

0111540423

taddese.tekletsadik@gmail.com,

21

ወ/ሮ አዲስ  አለም

የስነምግባር ና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት

0111540478

addisalemti@gmail.com

22

ወ/ሮ እታለማሁ ጥላሁን

 የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

0111223731

etaye1242@gmail.com

 

የሥራ ኃላፊዎች ስም የሥራ ድርሻና አድራሻ እንደ አስፈላጊነቱ የሚለዋወጥ በመሆኑ ወቅታዊ መረጃ በአገልግሎቱ ድረ ገጽ መከታተል ይቻላል፡፡

 

 

አድራሻ

ስድስት ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሃውልት

ፊት ለፊት በሚገኘው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ

ጉለሌ ክፍለ ከተማ

ወረዳ 2

ስልክ፡ +251-11-122-37-16

ፋክስ፡ +251-11-122-37-33/28

ድረ-ገጽ / ዌብሳይት፡ pppds.gov.et